የጀጎል ግንብን የማስዋብ ሥራ እየተከናወነ መሆኑ ተነገረ
Last Updated on Monday, 29 November 1999 19:00 Written by Admin1 Saturday, 14 August 2010 10:43
Source: Repoterበሐረር ከተማ የሚገኘውን የጀጎል ግንብ ታሪካዊነትና ቅርስነቱን ጠብቆ ለማቆየት፣ የመናፈሻ ቦታዎችን የመገንባትና የማስዋብ ሥራ እየተከናወነ መሆኑ ተጠቆመ፡፡ የሐረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት በጀጎል ግምብ ዙሪያ ሦስት የመናፈሻ ቦታዎችን በማዘጋጀት የማስዋብ ሥራ እያጠናቀቀ እንደሚገኝ ተጠቁሞ፣ አቧራማና ጭቃማ የነበረውን የጀጎል ግምብ ዙሪያና የውስጥ ለውስጥ መንገድ በኮብል ስቶን ንጣፍ መሸፈን መቻሉን የኢዜአ ዘገባ ያስረዳል፡፡ የጀጎልን ግምብ ሦስት ታሪካዊ በሮች ለማደስ ጨረታ ወጥቶ ሥራው ለኮንትራክተር መሰጠቱን ዘገባው ጠቁሞ፤ የፕሮጀክቱን 60 በመቶ ወጭ በዓለም ባንክ ቀሪው ደግሞ በክልሉ መንግሥትና በከተማ አስተዳደሩ እንደሚሸፈን ታውቋል፡

















