ለከተሞች የመሠረተ ልማት ፕሮግራም ለ19 ከተሞች የሚውል 150 ሚሊዮን
Last Updated on Tuesday, 03 November 2009 14:04 Written by Admin1 Friday, 30 October 2009 12:16
Repoter: Wednesday, 28 October 2009በብርቱካን ፈንታ
ለከተሞች የመሠረተ ልማት ማስፋፊያና አቅም ግንባታ ፕሮግራም ለ19 ከተሞች የሚውል 150 ሚሊዮን ዶላር የዓለም ባንክ ብድር መስጠቱን የሥራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር ገለፀ፡፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ከጥቅምት 13 እስከ ጥቅምት 16 ቀን 2002 ዓ.ም. በተለያዩ ዝግጅቶች ሲከበር የቆየውን የከተሞች ቀንን መጠናቀቅን አስመልክቶ በሥራና ከተማ ልማት ቢሮ የፖሊሲ ጥናትና ዕቅድ ማስተባበሪያ ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አብርሃም ተከስተ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደገለፁት በተገኘው ብድር አዲስ አበባ፣ ድሬዳዋና ሐረርን ጨምሮ በአራቱም ክልሎች የሚገኙ አራት ከተሞች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተናግረዋል፡፡
ገንዘቡ አዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ እና ሐረርን ጨምሮ ከአማራ ክልል፣ ባሕርዳር፣ ጐንደር፣ ደሴና ኮምቦልቻ፣ ከኦሮሚያ አዳማ፣ ቢሾፍቱ፣ ሻሸመኔና ጅማ፣ ከትግራይ መቀሌ፣ አዲግራት፣ ሽሬና አክሱም እንዲሁም ከደቡብ ክልል አርባምንጭ፣ ሶዶ፣ ዲላና ሐዋሣ መሆናቸውን ዶ/ር አብርሃም ተናግረዋል፡፡
ከባንኩ ከተገኘው ብድር በተጨማሪ “እያንዳንዳቸው ከተሞች 20 ከመቶ ማዋጣት ይጠበቅባቸዋል” ያሉት ኃላፊው ገንዘቡ የሚውለው ለከተማ መሠረተ ልማትና አገልግሎት ተብለው ለተለዩ ሥራዎች ሲሆን የአስፋልት ሥራን እንደማያጠቃልል ከከተሞቹ ጋር መስማማታቸውን አክለው ገልፀዋል፡፡
“ለበዓሉ ምን ያህል ወጪ አውጥታችኋል?” ተብሎ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ኃላፊው ሲመልሱ “ጥቃቅንና አነስተኛ ወጪ ያለው ዝግጅት ነው የተደረገው፡፡ በተጋነነ ወጪ የተከበረ ቀን አይደለም” በማለት ጥያቄውን አድበስብሰውት አልፈዋል፡፡
የከተሞች ቀን ለአራት ተከታታይ ቀናት ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ ከተማ የተከበረ መሆኑን የገለፁት ዶ/ር አብርሃም፣ ዓላማውም የከተማ ነዋሪዎችንና ባለ ድርሻ አካላትን ተሳትፎ በማጠናከርና መልካም ተሞክሮዎችን ማስፋፋት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ በተከበረው የከተሞች ቀን የተለያዩ ነገሮች መደረጋቸውን የገለፁት ኃላፊው፤ የከተሞች ትብብር መድረክ ጥቅምት 12 ቀን 2002 ዓ.ም. መመስረቱንና አዲስ አበባ ከተማ የትብብር መድረኩ ሊቀመንበር ሆና መመረጧን፤ 43 ከተሞች መሳተፋቸውን፣ በተለያዩ ገቢሮች ከተሞች ተወዳድረው አሸናፊዎቹ መሸለማቸውን አስታውሰዋል፡፡